በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ የአልጋ ቁራኛ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ተደረገላቸው።
እነዋሪ ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም የ(ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ)
በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የወረዳው ጤና ባለሙያዎች በጎነታችን ለጤናችን በሚል ሀሳብ የአልጋ ቁራኛ ለሆኑ ታማሚዎችን ቤት ለቤት በመጐብኘት ነፃ የህክምና አገልግሎት አደረገ።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ባለሙያዎች የተሰጠንን የሙያ አገልግሎት እናካፍል በሚል ተነሳሽነት ነፃ የህክምና አገልግሎት ስራ አስጀምረናል ሲሉ የሞረትና ጅሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ም/ ኃላፊ ወ/ሮ ጥሩነሽ አየለ ገልፀዋል።
አክለውም በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የጤና ሙያተኞች የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ታማሚዎችን ቤት ለቤት በመጐብኘት ነፃ የህክምና አገልግሎት የመስጠቱን ተግባር እና ሌሎች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቶችን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ገልፀዋል።
ነፃ የህክምና አገልግሎት የተደረገላቸው የአልጋ ቁራኞች ታማሚዎች እንደገለፁት አቅማቸው ወደ ጤና ጣቢያ ሄደው የሚታከሙበት ገንዘብ አለመኖራቸውን በመግለፅ ለሚደረገላቸው ነፃ የህክምና አገልግሎት በእጅጉ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።