”ባለ ብራንዱ የጅሩ ሰንጋ ”
እነዋሪ ፡ሐምሌ 4/2017ዓ/ም(ሞ.ጅ.ወ.መ.ኮ) በሰሜን ሽዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ከባለፉት አመታት ጀምሮ የጅሩ ሰንጋ በሚል ልዩ የንግድ ምልክት ወይም ብራንድ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የመጀመሪያው ወረዳ ነው።
የወረዳው በአርሶ አደሮች ለገበያ የደለቡ ሰንጋዎችን ከፋሲካ እና ከገና በዓል በተጨማሪ በከተማው ዘርፉ ለተሰማሩ ነጋዴዎች ጭምር ለገበያ እያቀረቡ ያለ ታታሪ አርሶ አደሮች ያሉበት ወረዳ ነው።
ጅሩ በሰንጋ አቅርቦቱ የታወቀ ቦታ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ሁሉ በጉጉት የሚጠብቁት አካባቢ ነው በነገው ለእለት በእለተ ቅዳሚ በእነዋሪ ከተማ በከብት ማድለብና በስጋ ዘርፍ የተሰማራው በአቶ በላቸው ነጋሽ (በኮኮብ መስክ ቁርጥ ቤት) የሐምሌ አቦን በዓል ምክንያት በማድረግ ለእርድ የቀረበው ባለ ብራንዱ የጅሩ ሰንጋ ይህንን ይመስላል።
በዚህ አጋጣሚ ድርጅቱ ለመላው የወረዳችንና የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ኑ ጅሩን በጋራ እናልማ


